
ስለ Fortify Forward Innovation Challenge
Fortify Forward Innovation Challenge 2024-2025 (FFIC) በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የማህበረሰብ ጤና እያሻሻለ ስውር ረሃብን ለመዋጋት እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረተን ለመግታት እንዲያግዝ የተዘጋጀ ተሸጋሪ ክልላዊ ውድድር ነው። ለከፍተኛ የኢንዱስትሪያዊ ምግብ ማጠናከርያ (LSFF) እና ባዮፎርቲፊኬሽን በፈጠራ የተሞሉ መፍትሄዎችን ለማግኘት በመፈለግ፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የፈጠራ ሰዎች እና ድርጅቶች በአፍሪካ አህጉር ወደ 500 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ እየጎዳ ላለው የምግብ የንጥረ ንገር ይዘት (ማይክሮኒዩትሬንት) እጥረት መፍትሔ ለመሻት በያዝነው በዚህ ተልእኮ እንዲቃቀሉን እንጋብዛለን።FAO: የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አካባቢያዊ ምልከታ።
በGAIN ስር ባሉት በLSFF፣ በBiofortification እና በNutrition Connect ቡድኖች የተዘጋጀው እና በተለያዩ አጋሮች ማለትም በ Waterloo Foundation፣ Funguo Program by United Nations Development Programme-Tanzania፣ DSM-Firmenich፣ NMB Foundation፣ Alliance of Biodiversity & CIAT እና University of Abomey Calavi-Benin ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ውድድር በምስራቅ እና ምእራብ አፍሪካ ውስጥ ባለው አጠቃላይ የምግብ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የምግቦችን የንጥረ ነገር ይዘት ጥራት ለማሻሻል የምናደርገው ከፍተኛ ጥረት አንድ አካል ነው።
በምግብ ማጠናከርያ (ፎርቲፊኬሽን) በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የመሰረታዊ ቫይታሚኖችን እና ማዕድኖችን ተደራሽነት የሚያረጋግጡ፣ ጠየናማ የንጥረ ነገር ይዘት ያላቸውን የተመጣጠኑ ምግቦች እና ጠንካራ የምግብ ስርዓቶቸን የሚያጎለብቱ መስፋፋት የሚችሉ ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማቅረብ እውቀትዎን እና የፈጠራ ችሎታዎን ይዘው ይምጡ።
በአፍሪካ ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን መዋጋት
በማይክሮኒዩትረንት ሁናቴ ላይ የተሰራው እና “ዘ ላንሴት” ላይ የታተመው በአይነቱ የመጀመርያው የሆነው ዓለም አቀፍ ጥናት በአሁኑ ወቅት ለሰው ልጅ ጤና የሚያስፈልጉትን 15 መሰረታዊ ማይክሮኒዩትረንቶች አፍሪካዊያን ምን ያህል በዝቅተኛ ደረጃ እያገኙ እንደሆነ ይፋ አድርጓል። ምስራቅ እና ምእራብ አፍሪካን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ያሉት የአፍሪካ ሀገራት በመላው ዓለም የቫይታሚን ኤ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ከሚታይባቸው አካባቢዎች አንዱ ናቸው። ይህ እጥረት ለዳፍንት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን በተለይም የህጻናትን እና የነፍሰ ጡር ሴቶችን የሞት መጣኔ አሳድጎታል። ለምሳሌ በአንዳንድ ክልሎች የቫይታሚን ኤ እጥረት ከ20-25 በመቶ በሚሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ እክል ይፈጥራል። (የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ አካባቢያዊ ምልከታ በአፍሪካ)
አሁኑኑ ያመልክቱ
የመወዳደርያ ዘርፎች
ዘርፍ I - የምግብ ማጠናከርያ (ፎርቲፊኬሽን) ትርፋማ እና ዘላቂ የንግድ ስራ ሞዴሎች/እቅዶች
የማሽን ዲዛይንን፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሳድን እና የሸማች የግንዛቤ ፈጠራ ዘመቻዎችን ጨምሮ የምግብ ማጠናከርያን የሚደግፉ አዋጭ የስራ ሞዴሎችን /እቅዶችን/ የሚያጎለብቱ ፈጠራዎች። ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡
- የማይክሮኒዩትረንት ጭማሪ (Micronutrient Addition): የፈጠራ ብቃትን በማሳየት መሰረታዊ ማይክሮኒዩትረንቶችን በከፍተኛ መጠን እና ጥራት መጨመር።
- ውጤታማ የማሽን ንድፍ: ይበልጥ ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የምግብ ማጠናከር ሂደትን የሚያሻሽሉ ማሽኖችን ማጎልበት።
- የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሳደግ: የሸማች ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ ወጪ ለመቀነስ እና የተጠናከሩ ምግቦችን ተደራሽነት ለማሳደግ ያሉትን የአቅርቦት ሰንሰለቶች ማጠናከር።
- የማትጊያ መዋቅሮች: የፋይናንስ፣ የቁጥጥር እና የገበያ ተኮር ማትጊያዎችን ጨምሮ ለዱቄት ፋብሪካዎች እና ለሌሎች አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያደርጓቸውን የንግድ ማትጊያዎችን መፍጠር።
ዘርፍ II - በባዮፎርቲፋይድ ሰብሎች ውስጥ የሰግሪጌሽን/አግሪጌሽን መፍትሔዎች
ባዮፎርቲፋይድ የሆኑ ሰብሎችን ከመደበኛ ሰብሎች መለየትን እና እነዚህን ሰብሎች ለገበያ ስርጭት ውጤታማ በሆነ መልኩ ማካተትን የሚመለከቱ መፍትሔዎች።
- የክትትል ደረጃዎች (Traceability Standards): ተለይተው መታወቃቸውን እና ባዮፎርቲፋይድ ካልሆኑ ሰብሎች በአግባቡ መለየታቸውን በማረጋገጥ የባዮፎርቲፋይድ ሰብሎችን ምንጭ ለመከታተል እና ለማረጋገጥ ዲጂታል መሳርያዎችን እና ደረጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ።
- ዲጂታል ፈጠራዎች (Digital Innovations): በባዮፎርቲፊኬሽን የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ክትትልን፣ የመረጃ አሰባሰብን እና የመስመር ላይ ክትትልን ለማሻሻል ቴክኖሎጂ መጠቀም/ስራ ላይ ማዋል።
- አዳዲስ የግብርና ፈጠራ ስራዎች (New Agricultural Interventions): የባዮፎርቲፋይድ ሰብሎችን ምርት እና ከእርሻ ወደ ገበያ የሚደረግ ስርጭትን የሚደግፉ አዳዲስ የግብርና አሰራሮችን ወይም ቴክኖሎጂዎችን ማጎልበት።
- የገበያ ትስስር (Market Interaction): ባዮፎርቲፋይድ ምርቶችን ስራ እና ሽያጭ ለማሻሻል በገበሬዎች እና በገበያዎች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር።
ዘርፍ III - ለምግብ ማጠናከርያ /Food Fortification/ ስራላይ የሚውሉ የፈጠራ ዘዴዎች
ከምግብ ዘይት እና ሩዝ እስከ ሻይ፣ ቡና እና የከብት ስጋ ድረስ ለምግብ ማጠናከርያ ምቹ የሆኑ ምርቶችን አይነት የሚያሰፉ እና እነዚህን ምርቶች በተሳካ ሁኔታ ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ የፈጠራ ዘዴዎችን የሚያጎለብቱ ተግባራዊ የሚደረጉ የስራ እቅዶች።
- አዳዲስ የምግብ አይነቶች (New Food Vehicles): እንደ ምግብ ዘይት፣ሩዝ፣ የከብት ስጋ፣ ሶስት ዙር የተጠናከረ ጨው፣ ሻይ እና ቡና ያሉትን ለመግብ ማጠናከርያ ስራ ምቹ የሆኑ አዳዲስ ምርቶችን ወይም የምግብ አይነቶችን መለየት እና ማጎልበት።
- የማጠናከር ሂደቶች (Fortification Processes): ውጤታማ እና ዘላቂ መሆናቸውን በማረጋገጥ እነዚህን አዳዲስ የምግብ አይነቶች ለማጠናከር ጥቅም ላይ የዋሉትን ዘዴዎች ማጎልበት።
- ምርት ማጎልበት (Product Development): የተጠናከሩ የምግብ አይነቶችን እና ሰብሎችን ብዛት እና አይነት መጨመር እና የማጠናከር ሂደቱን ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ ይዘቶችን ወይም ሂደቶችን መጠቀም።
ለአሸናፊዎች የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞች ምን ምንድን ናቸው?
የገንዘብ ድጋፍ
ለእያንዳንዱ አሸናፊ የስራ እቅድ ያቀረበውን አዳዲስ መፈትሄ ለማስፈጸም እና ለማስፋፋት የሚያግዘው የገንዘብ ልገሳ $5,000 ይሰጠዋል። አካባቢያዊ ዘላቂነት ላላቸው መፍትሄዎችም የሚሰጡ ልዩ ሽልማቶች አሉ!
ትምህርት
አሸናፊዎች ከስነ ምግብ፣ ከምግብ ስርዓቶች፣ ከንግድ ስራ ማጎልበቻ እና አግባብነት ካላቸው ሌሎች መስኮች መሪ ባለሙያዎች ጋር እንዲጣመሩ በማድረግ ከነሱ ስራ ጋር በቀጥታ ተያያዥ የሆነ የትምህርት ፕሮግራም እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህ ድጋፍ ያቀረቧቸውን መፍትሄዎች ይበልጥ እንዲያሻሽሉ እና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እንዲያሳድጉ ያግዛቸዋል።
የቴክኒክ ድጋፍ
ከማስተማር በተጨማሪ፣ አሸናፊዎች /ተሸላሚዎች) የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለማጠናከር እና ለገበያ ዝግጁ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው የተክኒክ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ይህም በምግብ ማጠናከርያ ሂደቶች፣ በስራ ማስፋፊያ እቅዶች እና በባዮፎርቲፊኬሽን ቴክኒኮች ላይ የሚደረግ ድጋፍን ሊያካትት ይችላል።
የመገናኛ ብዙሃን ተጋልጦ
አሸናፊ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች ብሎጎችን፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እና የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻዎችን ጨምሮ በGAIN የሚድያ ፕላትፎርሞች ላይ እንዲቀርቡ ይደረጋል። ይህ ተጋልጦ አሸናፊዎችን መታየት እንዲችሉ እና ገበያው ላይ አመኔታን እንዲያጎለብቱ ያግዛቸዋል።
የትስስር እድሎች
አሸናፊዎች በአፍሪካ ውሰጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በምግብ ማጠናከርያ (ፎርቲፊኬሽን) እና ባዮፎርቲፊኬሽን ላይ ከሚሰሩ የኢንዱስትሪ አመራሮች፣ ኢንቨስተሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ድርጅቶች መጠነ ሰፊ ኔትወርክ ጋር እንዲገናኙ ይደረጋል።
አቅም ግንባት
አሸናፊዎች በአውደ ጥናቶች እና በላቁ ስልጠናዎች በመታገዝ የፈጠራ ስራቸውን የረጅም ጊዜ ስኬታማነት በማረጋገጥ የአቅርቦት ሰንሰለትን በማሳደግ፣ በማርኬቲንግ ስልቶች እና በንግስ ስራ አመራር ዘርፎች ክህሎታቸውን ያጎለብታሉ።
አቻ ተወዳዳሪዎች ማወቅ
ይህን ውድድር ማሸነፍ ተዓማኒነትን ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚኖሩ ትብብሮች እና አጋርነቶች መንገዱን በመጥረግ በኢንዱስትሪው ውስጥ ካሉ አቻ ተወዳዳሪዎች ዘንድ እውቅና ማግኘትንም ያመጣል።
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ
ውድድሩ ካበቃ በኋላም፣ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ዘላቂነት እና መስፋፋት ለማረጋገጥ አሸናፊዎች ከGAIN እና ከአጋሮቹ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያገኛሉ።
በዓለም አቀፍ ፕላትፎርሞች ላይ መቅረብ
ለአሸናፊዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዓለም አቀፍ ባለ ድርሻ አካላት እና ኢንቨስተሮች የሚያቀርቡበትን እድል በመስጠት፣ አሸናፊ መፍትሄዎች አግባብነት ባላቸው ዓለም አቀፍ ፕላትፎርሞች እና ኮንፈረንሶች ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ።
በማህበረሰብ ጤና ላይ ተጽእኖ ማሳረፍ
በመጨረሻ አሸናፊዎች በምግብ ስርዓቶች እና በስነ ምግብ ዋስትና ላይ ዘላቂ ውርስ በማበርከት በአፍሪካ ውስጥ የማህበረሰብ ጤናን ለማሻሻል እና ስውር ረሃብን ለመግታት የሚደረገው የትልቁ ንቅናቄ አካል ይሆናሉ።
ብቁ ሀገራት








የውድድሩ አስፈላጊነት
የማይክሮኒዩትረንት እጥረቶች
ስውር ረሃብ ዝቅተኛ ገቢ በሚገኝባቸው የአፍሪካ ክልሎች ውስጥ የማህበረሰብ ጤና ስጋት ነው
2 ቢሊየን
በመላው ዓለም የችግሩ ሰለባ የሆነ ህዝብ ብዛት
የሚያስከትላቸው ችግሮች
እክል የተፈጠረበት የእውቀት እድገት፣ የተዳከመ በሽታን የመከላከል ስርዓት እና ከባድ በሽታዎች የመሳሰሉ የጤና ችግሮች
Fortify Forward Innovation Challenge በስፋት ለምግብ ፍጆታነት ጥቅም ላይ የሚውሉ ምግቦችን የንጥረ ነገር ይዘት ለማሻሻል በዘላቂ መፍትሄነት ኢንዱስትሪያዊ ማጠናከርያን እና ከፍተኛ ባዮፎርቲፊኬሽንን በማስፋፋት ለእነዚህ እጥረቶች መፍትሄ ለመስጠት አቅዷል።
የስራ ጥሪ : በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ህዝቦችም ከፍተኛ የንጥረ ነገር ይዘት ያላቸውን ምግቦች ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ አካባቢያዊ እውቀትን እና መስፋፋት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እውቀትዎን እና ሃሳቦችዎን ለማበርከት ይቀላቀሉን።
የብቁነት መስፈርት
የእጩ ተወዳዳሪ አይነት
አመልካቾች ታንዛኒያን፣ ኬንያን፣ ኡጋንዳን፣ ርዋንዳን፣ ኢትዮጵያን፣ ሞዛምቢክን፣ ቤኒንን እና ናይጄርያን ጨምሮ በምስራቅ እና ምእራብ አፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች መሆን አለባቸው። ብቁ የሆኑ አመልካቾች ስራ ፈጣሪዎችን እና ጀማሪዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና የትምህርት ተቋማትን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ተቋማትን (SMEs)፣ ምግብ አምራቾችን እና አቅራቢዎችን (ለምሳሌ ገበሬዎች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ ምግብ አቀነባባሪዎች) ያካትታሉ።
የተመዘገበ ኤጀንሲ ወይም ዜጋ የጭብጥ መጣጣም
አመልካቾች ጤናማ፣ ይበልጥ የተነጣጠኑ ምግቦችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው፣ እኩልነት የሰፈነበት እና የማይናወጡ የምግብ ስርዓቶችን ማጎልበት ከሚለው ከውድድሩ ራዕይ ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው። የሚቀርቡት መፍትሄዎች በምግብ ማጠናከር እና ባዮፎርቲፊኬሽን ላይ ማትኮር አለባቸው።
የጽንሰ ሃሳብ አዲስነት እድሜ ማረጋገጣ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ሁሉም አመልካቾች የውድድሩን ደንቦችና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ማንበብ፣ መረዳት እና መቀበል አለባቸው።
የማመልከቻዎች አነስተኛ መነሻ
ቢያንስ 1000 የተመዘገቡ ማመልከቻዎች ካሉ የምዝገባ መስኮቱ አይዘጋም። አዘጋጆች አስፈላጊ ከሆነ የምዝገባ ጊዜውን ሊያራዝሙ ይችላሉ። በቀረቡ ማመልከቻዎች ላይ የሚደረገው አሃዛዊ ያልሆነ ግምገማ (ለምሳሌ የመጀመርያዎቹ 50 ተመዝጋቢዎች ሁሉ የናሙና አዘገጃጀት) የጥራት ደረጃዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል።
በሀገር የሚኖር ውክልና
አዘጋጆቹ GAIN አፍሪካ ውስጥ ከሚሰራባቸው ስምንት ሀገራት፡ ታንዛኒያ፣ ቤኒን፣ ርዋንዳ፣ ሞዛምቢክ፣ ኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ናይጄርያ ከእያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ አንድ አሸናፊ ለመምረጥ የሚችሉትን ያህል ይሞክራሉ።
የጊዜ መርሐግብር
የመረጣ መስፈርት
-
የማይክሮኒዩትረንት ጭማሪ ጥራት (20%)፡
የተጨመሩ ማይክሮኒዩትረንትስ የስነ ምግብ ደረጃዎችን የማሟላት ጥራታቸውን እና ውጤታማነታቸውን መገምገም።
-
የማሽን ውጤታማነት እና ንድፍ (15%)፡
የምግብ ማጠናከር ሂደትን በብቃት እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በሚያሻሽል ማሽን ላይ የታከሉ ፈጠራዎችን /ኢኖቬሽንስ) መገምገም።
-
የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሳደግ (15%)፡
ወጪን ለመቀነስ፣ ሎጂስቲክስን ለማሻሻል እና የተጠናከሩ መግቦችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን መመርመር።
-
የማትጊያ መዋቅሮች (20%)፡
የቁጥጥር ወይም ገበያ ተኮር ማትጊያዎችን ጨምሮ የአምራቾችን የማትጊያ ስርዓቶች አዋጭነት እና ፈጠራ መገምገም።
-
የሸማች ግንዛቤ እና ፍላጎት (15%)፡
ተደራሽነት እና መስፋፋት የሚችል መሆኑ ላይ አጽኦት በመስጠት ሸማቾች የተጠናከሩ (ፎርቲፋይ የተደረጉ) ምግቦች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እና ፍላጎት ለማሳደግ የቀረቡ ስልቶችን መገምገም።
-
ኢኖቬሽን እና ፈጠራ (15%)፡
የስራ እቅዱን፣ የአጋርነቱን፣ የማርኬቲንግ እና የቴክኖሎጂ ትግበራዎችን አዲስነት ግንዛቤ ውስጥ ማስጋገባት።
በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች
የFortify Forward Innovation Challenge ግብ ምንድን ነው?
Fortify Forward Innovation Challengeን ስፖንሰር የሚያደርገው ማነው፣ ለምን?
በውድድሩ መሳተፍ የሚችለው ማን ነው?
የፈጠራ ስራው /ኢኖቬሽን/ ዋና ዋና ዘርፎች ምን ምንድን ናቸው?
ውድድሩ የሚሸፍናቸው የምግብ ማጠናከርያ እና ባዮፎርቲፋይድ ሰብሎች ገጽታዎች ምን ምንድን ናቸው?
ማመልከቻዬን ማቅረብ የምችለው እንዴት ነው?
ትብብሮች ይፈቀዳሉ?
ብቁ የሆኑት ምን አይነት የፈጠራ አይነቶች ናቸው?
Is there financial support for winning proposals?
How will proposals be evaluated?
የውድድሩ ፕሮግራም ምንድን ነው?
ማብራሪያ ለማግኘት ከአዘጋጆቹ ጋር እንዴት መገናኘት ይቻላል?
የአእምሯዊ ንብረት መብትን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?
ውድድሩ የሚያተኩርባቸው ማናቸውም አይነተኛ ሰብሎች ወይም ንጥረ ነገሮች አሉ?
ከአንድ በላይ የስራ ሃሳብ ማቅረብ እችላለሁ?
ለአሸናፊዎች የሚሰጠው የትምህርት ድጋፍ ምን አይነት ነው?
የቅድመ-ማቅረቢያ መረጃ መስጫ ፕሮግራም ይኖራል?
ለተሳትፎ ማናቸውም ክልላዊ መስፈርቶች አሉ?
ከውድድሩ በኋላ ምን ይከሰታል?
ያቀረብኩት የስራ እቅድ ባይመረጥ ምን ይከሰታል?
ደንቦች እና ሁኔታዎች
እባክዎ ሙሉ ደንቦቹን እና ሁኔታዎቹን እዚህ ያንብቡ
የለጋሽ እውቅና
ይን ንቅናቄ በጀርመን የፌደራል የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር (German Federal Ministry for Economic Cooperation and Development)፣ በኔዘርላንድስ የውጪ ጉዳይሚኒስቴር (Ministry of Foreign Affairs of the Netherlands)፣ በአውሮፓ ህብረት (European Union)፣ በግሎባል አፌርስ ካናዳ (Global Affairs Canada) በኩል በካናዳ መንግስት፣ በDevelopment Cooperation and Africa Division (DCAD) በኩል በIrish Aid እና በSwiss Agency for Development and Cooperation (SDC) of the Federal Department of Foreign Affairs (FDFA) ጣምራ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የNourishing Food Pathways ፕሮግራም አንድ አካል ነው። በዚህ ውስጥ ተካተው የቀረቡት ግኝቶች፣ ሃሳቦች እና መደምደሚያዎች የጸሀፊዎቹ ሲሆኑ የማናቸውንም የGAINን ለጋሽ አጋሮች አቋም ወይም ፖሊሲ አያንጸባርቁም።